ሱዳን የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የአረብ ሊግ የግብፅን አቋም በመደገፍ ያወጣውን የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አደረገች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአረብ ሊግ ሀገራት የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ግብፅን አቋም በመደገፍ ያወጣውን የውሳኔ ሀሳብ ሱዳን ውድቅ ማድረጓ ተገልጿል።
የግብፅ መንግስት በካይሮ በተካሄደው 153ኛ የዓረብ ሊግ ሀገራት የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ነው በህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ የሊጉ አባል ሀገራት ከሱዳን እና ከግብፅ ጎን እንዲሆኑ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበው።
ሱዳን በበኩሏ በግብፅ በኩል የቀረበውን የዓረብ ሊግ ድጋፍ የውሳኔ ሀሳብ ውድቅ አድርጋለች።
ስሟም ከዚህ ጋር ተያይዞ እንዲነሳ እንደማትፈልግ በይፋ ያስታወቀችው ሱዳን፥ የውሳኔ ሀሳቡ ብሄራዊ ጥቅሟንም የሚጎዳ እንደሆነም ገልፃለች።
የዓረብ ሊግ ሀገራት በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር አለመግባባት ውስጥ ጣልቃ እንዳይገቡም ፍላጎቷ መሆኑንም ሱዳን ገልፃለች።