Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በአይ ኤም ኤክስ ፍራንክፈርት 2022 አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዓለም ትልቅ የቱሪዝም መድረክ በሆነው አይ ኤም ኤክስ ፍራንክፈርት 2022 አውደ ርዕይ ላይ እየተሳተፈች ነው።

በቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ የተመራ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ እና ትስስር ለመፍጠር ጀርመን ፍራንክፈርት ይገኛል።

የቱሪዝም ዘርፉን ስኬታማ ለማድረግ ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት የሆኑትን የግል የኹነት ስብሰባ እና ኤግዚብሽን አዘጋጆችን፣ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፎር አፍሪካ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ታዋቂ ባለኮከብ ሆቴሎች በማስተባበር የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮን እና ማይስ ኢትዮጵያ ብራንድ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያስተዋወቁ መሆኑ ተገልጿል።

አይ ኤም ኤክስ ፍርንክፈርት 2022 ለኹነት ኢንዱስትሪ ተዋንያን እና ባለድርሻ አካላት ስራ ትስስር እና ስኬት በዓለም አቀፍ ደረጃ በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ አውደ ርዕይ መሆኑ ተመላክቷል።

የቱሪዝም ሚኒስትሯ ናሲሴ ጫሊ በፖሊሲ ፎረም የተሳተፉ ሲሆን÷ከአይ ሲ ሲ ኤ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በተጨማሪም ከኬንያ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ከሩዋንዳ ቱሪዝም ሚኒስትሮች እና የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተናጠል የሁለትዮሽ ስምምነት ማድረጋቸው ን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ልዑኩ በቱሪዝም ሚኒስቴር መሪነት የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ እና ማይስ ኢትዮጵያ ብራንድ በዓለማችን ትልቅ የኹነት ቱሪዝም መድረክ በሆነው በአይ ኤም ኤክስ ፍራንክፈርት 2022 መገኘቱ ለአገር ኢኮኖሚ የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው ተብሏል፡፡

በፕሮግራሙ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ150 በላይ የአገራት ተወካዮች፣ ከ3 ሺህ 817 በላይ የኹነት ኢንዱስትሪው አገልግሎት ገዢዎች፣ ከ2 ሺህ 500 በላይ ከተለያዩ አገራት እና ድርጅች የተውጣጡ የኹነት አገልግሎት አቅራቢዎች እንዲሁም በዘርፉ የግል፣ የመንግስትእና ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.