Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር እየተወያዩ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር እና የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር እየተወያዩ ነው።

በውይይታቸውም ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል የአፍሪካ አገራት የዩክሬን እና ሩሲያ ግጭት ተፅዕኖ ውስጥ ስለመሆናቸው ለፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አብራርተዋል፡፡

ፕሬዚዳን ማኪ ሳል ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫም÷ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር የሚያደርጉት ውይይት ተቋርጦ የነበረውን የእህል ምርት እና የአፈር ማዳበሪያ ወደ አፍሪካ እንዲገባ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑ ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል ያለውን ግጭት ለመፍታት የሚያስችል ውይይት እንደሚያደርጉም ሲጅቲኤን በዘገባው አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.