Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር ዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የዋንጫ አቀባበል ሥነ-ሥርዓት በአዳማ ተካሄደ፡፡

የአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ የአዳማ ከተማ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፣አባ ገዳዎች፣ ሃደ ስንቄዎች እንዲሁም የተለያዩ የማኀበረሰቡ ክፍሎች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል።

በመክፈቻ መርሃ-ግብሩ ላይ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዴ፥ ግድቡ የሀገራችን ሉዓላዊነትና የአንድነታችን ምልክት ነው ያሉ ሲሆን ግድቡ በዜጎች ተሳትፎ እንደተጀመረው ሁሉ በዜጎች ጉልበት፣ ሐብት እና አቅም በመጨረስ ለዓለም ተምሳሌት እንሆናለን ብለዋል።

የአዳማ ከተማ ነዋሪዎችና ባለሐብቶችም በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በግንባር ቀደምትነት በመሳተፍ ያሳዩትን ላቅ ያለ ተሳትፎ ለግድቡ መሳካትም በማበርከት የድርሻቸውን እንዲወጡ መልዕክት ማስተላለፋቸውንም ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.