1ሺህ 30 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በሶስት ዙር 1 ሺህ 30 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ።
ከእነዚህ ውስጥ 209 ሴቶች 68 ህጻናትና 753 ወንዶች መሆናቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 34 ሺህ 328 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡