Fana: At a Speed of Life!

የክህሎት ስልጠና እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት እድልን ለማስፋፋት የሚያስችል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በክህሎት ስልጠናና የስራ ዕድል ፈጠራን አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል ውይይት እያካሄዱ ነው።

ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ በጄኔቫ እየተካሄደ ካለው ዓለም አቀፍ የሥራ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን የሁለትዮሽ እና የባለ ብዙ ዘርፍ ግንኙነቶችን አጠናክረን ለመቀጠል የሚያስችል በተለይም የክህሎት ስልጠና እና የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕድልን ለማስፋፋት የሚያስችል ውይይት እያካሄድን ነው ብለዋል።

ከኳታር የሥራ ሚኒስትር ጋር በሁለቱ እህትማማች ሀገራት ግንኙነት በተለይም በክህሎት ስልጠናና የስራ ዕድል ፈጠራ አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል  ውይይት መካሄዱንም ገልጸዋል።

አሁን ባለው የስራ ስምሪት አካሄድ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን ለይተን በተለያዩ መስኮች የሰለጠነ የሰው ሃይል ወደ ስራ ለማሰማራት የምንችልበትን እንዲሁም አዳዲስ የስራ ዕድልን የምንፈጥረበት ሁኔታ ላይ ቀጣይነት ያለው ምክክር ለማድረግ ተስማምተናልም ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

በተጨማሪም የኳታር መንግስት በቅርቡ ለሚያካሂደው የእስያ-አፍሪካ የምክክር መድረክ ኢትዮጵያ ከተመረጡ አስር የአፍሪካ ሀገራት አንዷ በመሆኗ እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ እና ሀገራት የፍልሰተኞች ጉዳይ የሚኒስትሮች ፎረም ሊቀመንበር በመሆኗ በምክክር መድረኩ ላይ የቀጠናውን ሀገራት አስተባብራ እንድትገኝ  ግብዣ ቀርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.