Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ የልማት ኢኒሼቲቮች የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ነው – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የልማት ኢኒሼቲቮች እና ንቅናቄዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ይገኛሉ አሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ።

የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች በፓርቲው የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ ተወያይተዋል።

አቶ አደም ፋራህ በወቅቱ እንዳሉት÷ ባለፉት ወራት በተሰሩ ጠንካራ ስራዎች የፓርቲውን ተቋማዊ አቅም በማጠናከር ከብዛት ወደ ጥራት ማሸጋገር ተችሏል።

የፓርቲው የልማት ኢኒሼቲቮች እና ንቅናቄዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ይገኛሉ ብለዋል።

በዚህም የሌማት ትሩፋት፣ አረንጓዴ ዐሻራ፣ የከተማና ገጠር ኮሪደር ልማት፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የበጋ ስንዴ ልማት፣ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያ የመሳሰሉት ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረገ ውጤት ማምጣታቸውን አመልክተዋል።

በመላዉ ሀገሪቱ ከ11 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት መደረጉን ጠቅሰው÷ በውይይቱ የህዝቡን ጥያቄ በማዳመጥ ፓርቲው ምላሽ መስጠት መቻሉን አስገንዝበዋል፡፡

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ እና ቅቡልነት ያለዉ እንዲሆን እንዲሁም ፓርቲው የጠራ ሀሳብ ለህዝብ አቅርቦ አብላጫ ድምፅ አግኝቶ እንዲመረጥ ድርብ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.