Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩን ዛሬ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ አስጀመረ፡፡

መርሐ ግብሩ ” አሻራችንን ፣ ለትውልዳችን ፣ለትውልድ እንስራ ፣ ለኢትዮጵያ እንትከል በሚል መሪ ቃልና መልዕክቶች ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የአዲስ አበባ የብልፅግና ፖርቲ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ይመር ከበደ እንደገለፁት ፥ ” አረንጓዴ አሻራን ስናኖር የነገ ትውልድንና የበለፀገች ኢትዮጵያን የማፅናትና የማበልፀግ አጀንዳ በመሆኑ በንቃት መሳተፍ ይገባል ።

አያይዘውም ፥ እኛ ትናንት በተሰራው እየኖርን ስለሆነ ለነገ ትውልድ መስራት አለብን ፤ ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው በመሆኑ መትከል ፣ መንከባከብ ፣ ማሳደግና መጠቀም ይኖርብናል ነው ያሉት፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በበኩላቸው ፥ አሻራችንን በማጉላት ችግኞቻችንን በመትከልና ሰላማችንንና ፀጥታችንን በማክበር የጀመርነውን የከተማችንና የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ እውን እናደርጋለን ብለዋል ።

ቢሮው በከተማ ደረጃ 1ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ያቀደ ሲሆን ፥ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ከተዘጋጁ 20ሺህ የችግኝ ጉድጓዶች ዛሬ 5ሺህ ችግኞች መተከላቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.