Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል እየተስፋፋ ያለው ሕገወጥ የነዳጅ ዝውውርና ስወራ በተጠቃሚዎች ላይ ጫና መፍጠሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ከተማና ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች እየተስፋፋ ያለው ሕገወጥ የነዳጅ ዝውውርና ስወራ በተጠቃሚዎች ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስተወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኦኬሎ ኡቦንግ ÷ሕገወጥ የነዳጅ ዝውውርና ስወራ ወንጀልን ለመግታት 22 አባላት ያሉት ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል።

ግብረ ኃይሉ በትናንትናው ዕለት ብቻ በጋምቤላ ከተማ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከ15 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ በቤት ውስጥ ሰውረው የተገኙ ስድስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ነው የገለጹት።

ችግሩ እየተስፋፋ የመጣው የነዳጅ ማደያዎች ከሕገወጥ ነዳጅ አዘዋዋሪዎች ጋር በመመሳጠር በምሽት ነዳጅ ቀድተው ስለሚሰጧቸው እንደሆነም ኃላፊው አስረድተዋል።

የተያዘው ነዳጅ ከየትኞቹ ማደያዎች እንደተቀዳ በማጣራት እርምጃ ለመውስድ እየተሰራ እንደሆነ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

ከአዲሱ የነዳጅ ስርጭት መመሪያ ጋር ተያይዞ በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ ለመሰወር የሚሞክሩ ህገ ወጦች በመበራከታቸው ችግሩን ለመግታት የህዝቡና የጸጥታ አካላት ድጋፍና ትብብር ሊጠናከር እንሚገባ አቶ ኦኬሎ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.