Fana: At a Speed of Life!

ጃፓን በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የሚወጣ የምግብ እህል ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን መንግሥት በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር የሚወጣ የምግብ እህል ድጋፍ ማድረጓን አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሑፍ÷ የጃፓን መንግሥት በፈረንጆቹ ከባለፈው ታህሳስ ጀምሮ እስከ ሐምሌ ወር ድረስ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 7 ሺህ 600 ሜትሪክ ቶን የምግብ እህል ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል፡፡

ለዚህም 6 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡

በዓለም የምግብ ፕሮግራም በኩል በተሰራጨው በዚህ ድጋም÷በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ 446 ሺህ በላይ ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ማዳረስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.