Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 631 የፖሊስ መኮንኖች እያስመረቀ ነው።
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በማስመረቅ ላይ የሚገኘው ሰልጣኞች በሁለተኛ ዲግሪ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በዲፕሎማ እንዲሁም በሰርቲፊኬት ያሰለጠናቸው ሲሆኑ፥ ሰልጣኞቹም በፖሊሰ ሳይንስ፣ በሥነ-ወንጀልና ወንጀል ፍትህ፣ በወንጀል ምርመራ እንዲሁም በፖሊስ መኮንንነት ዘርፍ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
በተጨማሪም ከምረቃ መርሐ ግብሩ ጎን ለጎን ለከፍተኛ አመራሮች የማዕረግ ዕድገት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመ 75 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፥ በቅርቡም ከኮሌጅነት ወደ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማደጉን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.