Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ተወላጅ ዳያስፖራ አባላት በነበረው የፀጥታ ችግር ለተጎዱ የፀጥታ አካላት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ተወላጅ የሆኑ የዳያስፖራ አባላት በጋምቤላ ከተማ በነበረው የፀጥታ ችግር ጉዳት ለደረሰባቸው የፀጥታ አካላት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የድጋፉ አስተባባሪ ኢንጂነር የን ሪያንግ ÷ የተደረገው ድጋፍ ከ100 ሺህ ብር በላይ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይም በክልሉ በሚከናወኑ የልማትና የሰላም ስራዎች በንቃት እንደሚሳተፉ ገልፀዋል።
የፀጥታ አካላት የአገራችውን ክብር በማስቀደም ለከፈሉት መስዕዋትነት በታሪክ ይታወሳሉ ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የክልሉ ዳያስፖራ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኦኬሎ ኮም በበኩላቸው÷ የዳያስፖራ አባላቱ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀው÷ ለዚህም የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው የፀጥታ አካላትና የተጎጂ ቤተሰቦች ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.