Fana: At a Speed of Life!

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ በርካታ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በ2014 በጀት ዓመት በብዙ ፈተናዎች ውስጥ በርካታ አመርቂ ውጤቶች መመዝገባቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡
የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ እና መንግስት የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም እና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ በ2014 በጀት ዓመት የኦሮሚያ ክልል በርካታ ችግሮችንና ፈተናዎችን ያስተናገደ መሆን አስታውሰዋል፡፡
ይሁን እንጂ በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በሰሩት ስራ በተለያዩ ዘርፎች አመርቂ ውጤት መመዝገቡን አስገንዝበዋል፡፡
የተፈጠሩ ፈተናዎች ወደ ድል የሚቀይር፣ በሁኔታዎች የማይሸበር እና ለዓላማው መስዋዕት የሚሆን አመራር በማፍራት የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡
የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር እና ለሌሎች ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትም የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የበለጠ ለማስቀጠል በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡
በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን እና የብልጽግናን ጉዞ እውን ለማድረግ ወጣቶችን የማሳተፉ ሒደት በቅንጅት እንደሚሰራ መገለጹን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሚቀጥለው በጀት ዓመትም የአመራሮችን የፖለቲካ ክህሎትና ግንዛቤ በማጎልበት ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር ጥረት እንደሚደረግም ተመላክቷል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.