Fana: At a Speed of Life!

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል÷ 63 ነጥብ 9 በመቶ ያህሉ 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ቢሮው አስታውቋል፡፡
ይህም ካለፉት ዓመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን ተገልጿል፡፡
ስለሆነም ተማሪዎች ውጤታቸውን ቀጥሎ ያለውን ሊንክ በመጫን https://aaceb.gov.et/%E1%8B%A88%E1%8A%9B-%E1%8A%AD%E1%8D…/ ወይም http://aaceb.gov.et በመጠቀም ሬጅስትሬሽን ቁጥር በማስገባት እና GO የሚለውን በመጫን ኦላይን ማየት እንደሚችሉ ቢሮው አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ 71 ሺህ 832 ተማሪዎች የስምንተኛ ክፍል ፈተና መውሰዳቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.