Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል በተለያዩ ዞኖች በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው የውሃ አውታሮች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች በግጭት ምክንያት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የውሃ አውታሮች ጥገና ተደርጎላቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
በግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን የውሃ አውታሮች ወደ ነበሩበት ለመመለስ÷ የውሃ ፓምፖች፣ ጄኔሬተሮች እና የውሃ ማጣሪያ ኬሚካሎችን በመለገስ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ መደረጉን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.