የመዲናዋ አስተዳደር ከጃፓኑ ኩባንያ ጋር የ360 ሚሊየን ብር የግዢ ውል ስምምነት ተፈራረመ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፊርማ ሥነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የኢትጵያና ጃፓን ግንኙነት ከ90 ዓመታት በላይ የቆየ መሆኑን ጠቁመው÷ ወሳኝ በሆኑ የትምህርት እና የቴክኖሎጂ ዘርፎች የሚያደርጉትን ድጋፍ አድንቀዋል።
ዛሬም ያልተቋረጠ ድጋፍቸው ለከተማችን በትራንስፖርቱ ዘርፍ ወሳኝ በሆነው መንገድ ጥገና በሚጠቅም መሳሪያ ግዥ ደግፈውናል ብለዋል።
ድጋፉ በኢዲስ አበባ የተሻለ የመንገድ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያግዝ የገለጹት ከንቲባ አዳነች÷ አቅራቢ ድርጅቱም በወቅቱ እንደሚያቀርብ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡