ኢትዮጵያ የምታካሂደው የአካባቢ ጥበቃ ስራ ድንበር ተሻጋሪ ሚና እንዳለው ምሁራን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ የምታካሂደው የአካባቢ ጥበቃ ስራ ድንበር ተሻጋሪ ሚና እንዳለው የዘርፉ ምሁራን ተናግረዋል፡፡
ዓለም በአየር ንብረት ለውጥ በምትሰቃይበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው የአረንጓዴ አሻራ ልማት ዘመኑን የዋጀ መሆኑን ነው ምሁራኑ የገለጹት፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህሩና የአየር ንብረት ተመራማሪው ፕሮፌሰር በላይ ስማኔ እና የወርልድ ሪሶርስ ኢንስቲትዩት ተመራማሪው ዶክተር ኤርሚያስ አባተ÷ የአካባቢ ጥበቃ ስራ የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ ዘላቂ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሁነኛው መፍትሄ መሆኑን አስረድተዋል።
የውጪው ዓለም ለዚህ ዓለም አቀፋዊ ትሩፋት ላለው ተግባር ዕውቅና ነፍገውታል ያሉት ምሁራኑ÷ ይህም ያላቸውን የተዛባ አተያይ የሚያመላክት ነው ብለዋል።
ምሁራኑ ባደረጉ ሀገራት ሳቢያ እያጋጠመ ያለውን ችግር ለማለፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ምዕራባውያን ቢደግፉም ባይደግፉም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የተጀመረው የአካባቢ ጥበቃ ስራ ዘላቂና የሚፈለገውን ውጤት እንዲያስገኝም ከዘመቻ ባሻገር መርሐ ግብሩን ተቋማዊ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት፡፡
በመሀመድ አሊ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!