Fana: At a Speed of Life!

ፈተናዎች ሊያጠነክሩን እና የበለጠ ሊያተጉን እንጂ ሊሰብሩን ቀርቶ ሊያጎብጡን አይችሉም-የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈተናዎች ሊያጠነክሩን እና የበለጠ ሊያተጉን እንጂ ሊሰብሩን ቀርቶ ሊያጎብጡን አይችሉም ሲል የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የ2014 በጀት ዓመት የመንግሥት የሥራ ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል፡፡
ፓርቲው ግምገማውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫም ÷የኢትዮጵያ የከፍታ ጉዞ የማይመቻቸው የውጪ እና የውስጥ ኃይሎች ተቀናጅተው የከፈቱትን ዘርፈብዙ ዘመቻ በፅናት ታግለን የብልፅግና ጉዟችን አስቀጥለናል ብሏል፡፡
ለዚህም በክልሉ የ2014 በጀት ዓመት የመንግሥት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እንደታየው በርካታ ፈተናዎችን በቁርጠኝነት ታግሎ በመርታት በክልሉ አንፃራዊ ሠላምና ፀጥታ ለማስፈን እና ስኬታማ የልማት ድሎችን ለማስመዝገብ መቻሉ አንዱ ማሳያ መሆኑን አውስቷል፡፡
ክልሉ ኢትዮጵያን ከሁለቱ ሱዳኖች የሚያዋስን እና በማዕድን ሃብቱ የካበተበመሆኑ በምሥራቅ አፍሪካ ጂኦ-ፖለቲካዊ ሁነቶች ውስጥ የራሳቸውን ሚና ለመጫዎት በሚፈልጉ ኃያላን ሀገራት ጭምር በተለየ ሁኔታ የሚታይ ቀጠና መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
ዛሬም ሆነ ነገ በበርካታ ፈተናዎች ልንፈተን እንችል ይሆናል ያለው መግለጫው÷ ይሁን እንጂ እነዚህ ፈተናዎች ሊያተጉን እና የበለጠ ሊያጠነክሩን ካልሆነ በቀር ሊሰብሩን ቀርቶ ሊያጎብጡንአይችሉም ሲል አስገንዝቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.