ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም÷ የሁለቱን አገራት የቆየ ወዳጅነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡
በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ሰርጌይ ላቭሮቭ ትናንት አዲስ አበባ ሲገቡ÷ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ላቭሮቭ÷ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት እያደረጉ ይገኛል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በግብጽ፣ በኮንጎ ብራዛቪልና በኡጋንዳ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
በወንደሰን አረጋኸኝ
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!