በአሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ላይ እየተወሰደ የሚገኘው የተቀናጀ እርምጃ በአኩሪ ድል ታጅቦ ቀጥሏል-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
አዲ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ላይ እየተወሰደ የሚገኘው የተቀናጀ እርምጃ በአኩሪ ድል ታጅቦ መቀጠሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ የአልሸባብ የሽብር ቡድን በኤልከሬ ወረዳ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት ከሌላኛው የሽብር ቡድን ከሸኔ ጋር ለመገናኘት አልሞ የነበረ ቢሆንም ይህ እቅዱ ሙሉ በሙሉ መክሸፉን አረጋግጧል።
በተቀናጀው የመልሶ ማጥቃት እርምጃም የተበታተነውንና ተቆርጦ የቀረውን የሽብር ቡድኑ ኃይል ላይ የሚወሰደው የማጽዳት ተልእኮ በተቀናጀና በተናበበ መልኩ እንደሚቀጥል ነው ያስታወቀው።
የሽብር ቡድኑ ይዞት የመጣውን የሽብር ተልእኮ ሙሉ በሙሉ በማክሸፍና አሁንም ገብቶባቸው ከነበሩት አካባቢዎች በማጽዳቱ ሂደት ከጸጥታ ኃይሉ ባሻገር፥ የአካባቢው ሕዝብ አስተዋጽኦና መስዋእትነት ከፍተኛ የነበረ መሆኑን አውስቶ፥ ይህ ቡድን ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሕዝቡ የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መንግስት ጥሪውን ያቀርባል ብሏል።
የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦