ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭን በጽሕፈት ቤታቸውን ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ኢትዮጵያና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በሚያጠናክሩባቸው ዘርፎች ላይ መክረዋል፡፡
ከውይይቱ በኋላም የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫው÷ በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተዳሰዋል።
በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ትናንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።
ላቭሮቭ አዲስ አበባ ሲገቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!