Fana: At a Speed of Life!

ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የላቦራቶሪ አገልግሎትን ማዘመን እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የላቦራቶሪ አገልግሎትን ማዘመንና ማሻሻል እንደሚገባ የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ ተናገሩ፡፡

የአማራ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አጠቃላይ የላቦራቶሪ አገልግሎት ማስተዋወቂያ ልዩ አውደ ርዕይ አዘጋጅቷል፡፡

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ  አውደ ርዕዩን አስመልክተው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የላቦራቶሪ አገልግሎትን ማዘመንና ማሻሻል ያስፈልጋል።

በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት በሰለጠነ የሰው ኃይል በቂ የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤትን በፍጥነት ለመከወን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ  ገልጸዋል፡፡

አውደ ርዕዩ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እየሰጣቸው የሚገኙ የላቦራቶሪ  አገልግሎቶችና በስሩ የሚገኙ የጤና ተቋማት ልዩ ተሞክሮዎችን ለማስተዋወቅ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአውደ ርዕዩ አጋር ድርጅቶች በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅዖ የሚያበረክቱ የላቦራቶሪ ቴክኖሎጂዎችን እንዲያስተዋውቁ የሚያስችል መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ በላቦራቶሪ አገልግሎት የተሻለ አገልግሎትና ልዩ ልዩ ድጋፍ ላደረጉ ግለሰቦችና ተቋማት ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.