Fana: At a Speed of Life!

ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ላቭሮቭ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

በዛሬው እለትም ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር የሁለቱን አገራት የቆየ ወዳጅነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል፡፡

እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር የተወያዩ ሲሆን፥ ከውይይቱ በኋላ በሰጡት የጋራ መግለጫ፥ አቶ ደመቀ መኮንን በውይይታችን በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ያለንን ግንኙነት አጠናክረን ለመቀጠል መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡

ከውይይታቸው በኋላ፥ አቶ ደመቀ መኮንን እና ሰርጌይ ላቭሮቭ በሩስያ ኤምባሲ ችግኝ ተክለዋል።

ዛሬ ከሰዓትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለሚኒስትሩ ሽኝት እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.