Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በአንድ ጀንበር 100 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሔደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በአንድ ጀንበር 100 ሚሊየን ችግኝ መትከል የሚያስችል መርሐ ግብር በስልጤ ዞን ምስራቅ ስልጢ ወረዳ ተጀምሯል።

የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ፣ የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን፣ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እና ሌሎች የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በክልሉ 1 ቢሊየን ልዩ ልዩ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን ፥ በዛሬው ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ እንደሚገኙ ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአንድ ጀንበር 100 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ ተሳታፊ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉት ፥ አስከፊውን የድህነት ታሪክ ለመታገል አንድነታችንን ማጠናከርና በልማት ስራችን ላይ መትጋት ዓብይ ጉዳያችን ነው።

አሁን ላይም በምስራቅ ስልጢ ወረዳ በትንሹ አባያ ሀይቅ ዳርቻ የሙዝ ችግኞች እየተተከሉ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.