Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ልማት ፈንድ ለኢትዮጵያ የ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪክ ልማት ፈንድ ዳይሬክተሮች ቦርድ ለኢትዮጵያ የ4 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማጽደቁን አስታውቋል፡፡
ድጋፉ በኢትዮጵያ በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም እና በምርምር እና ፖሊሲ ትንተና ላይ ያለውን አቅም ማጠናከር እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
የተደረገው ድጋፍ በገንዘብ ሚኒስቴር አማካኝነት የሚተገበር መሆኑንም ከአፍሪካ ልማት ፈንድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የአፍሪካ ልማት ፈንድ የአፍሪካ ልማት ባንክ አንዱ ቅርንጫፍ ሲሆን፥ ለአፍሪካ ሀገራት የፋይናንስ ድጋፍ ያደርጋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.