የአትሌቶቻችንን የላብ ውጤት የሀገር ክብር መገለጫ በሆነው ሰንደቃችን ላይ አሻግረን እንድናይ አድርጎናል – አቶ ርስቱ ይርዳ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌቶቻችንን የላብ ውጤት የሀገር ክብር መገለጫ በሆነው ሰንደቃችን ላይ አሻግረን እንድናይ አድርጎናል ሲሉ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ በአትሌቲክስ ቡድኑ የተገኘውን ዉጤት አስመልክቶ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት እንደገለጹት÷ አትሌቶቻችን በአሜሪካ ኦሪገን ሲካሔድ በቆየው 18ኛው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ባደረጉት ብርቱ ጥረት እውነተኛ የሀገር ፍቅር ስሜትን ተላብሰው የአገራቸውን ክብር በማስቀደም በዓለም አደባባይ ከፍ ብለን እንድንታይ አድርገውናል።
ከተባበርን እና አንድነታችንን ካጸናን ምን ያህል ተጽዕኖ መፍጠር እንደምንችል አንዱ ማሳያ የጀግኖቻችን ትጋት ነውም ብለዋል።
ዛሬ በሁሉም መስክ እየገጠመን ያለውን ፈተና ልክ እንደ አትሌቶቻችን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ለድል የምንበቃበት እና የሀገራችንን የቀደመ ታሪኳን የምናድስበት ቀን ሩቅ አይደለም ነው ያሉት።
የዓላማ ጽናት ጥልቅ የሀገር ፍቅር ስሜት በአትሌቶቻችን ላይ እንዳየነው ሁሉ የሀገርን ክብር እና የቀደመ የጀግንነት ታሪካችንን ማስቀጠል የዚህ ትውልድ ድርሻ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በልጆቻችን መንፈሰ ጠንካራነት ምክንያት የዓለም ህዝብ ሙሉ ትኩረት አግኝተናል ብለዋል ርዕሰ መስተዳደሩ።
በተገኘው ድል ለጀግኖች አትሌቶች፣ ለስፖርት ልኡካን ቡድኑ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ለስፖርት ቤተሰቡ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!