Fana: At a Speed of Life!

የተተከሉ ችግኞችን ህብረተሰቡ እንደ ልጅ ሊንከባከባቸው ይገባል – ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተተከሉ ችግኞች ህብረተሰቡ እንደ ልጅ ሊንከባከባቸው ይገባል ሲሉ በጎንደር ከተማ ተገኝተው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የተሳተፉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሐብታሙ ኢተፋ ገለጹ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የልዑካን ቡድን በጎንደር ከተማ የችግኝ ተከላ አካሂዷል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የተገኙት ሚኒስትሩ ፥ ችግኝን ተክሎ መንከባከብና ማሳደግ ህፃናትን ወልዶ እንደማሳደግ ይቆጠራል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ ደግሞ በከተማዋ ባለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው ፥ በተያዘው የክረምት ወራት በከተማዋ በሁሉም አካባቢዎች ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ገልፀዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የከተማዋ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የልዑካን ቡድኑ ጎንደር ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ቤተሰብ ላላቸው ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፉ በከተማው ለሚገኙ 150 ተማሪዎች ሲሆን ፥ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራው ልዑክ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ በተገኙበት አስረክበዋል።

ድጋፉ 500ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን ፥ መፅሐፍት፣ ደብተር፣ እርሳስ እና እስክርቢቶን አካቷል።

በምንይችል አዘዘው

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.