በደብረ ታቦር ከተማ በ160 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ታቦር ከተማ በ160 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡
በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የመሰረተ ልማት ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃብታሙ ጌታሁን በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት÷ለመሰረተ ልማት ግንባታ ትኩረት በመስጠት ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
በዚህም ባለፈው በጀት ዓመት የተገነቡ 5 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮብል ስቶንና የ10 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ፣ የውሃ ማፋሳሻ ቦይ፣ የሼድ ግንባታና የእግረኛ መንገድና ሌሎች ፕሮጀክቶች ዛሬ ተመርቀዋል ብለዋል።
የተገነቡት የመሰረተ ልማቶች ህብረተሰቡ ለዘመናት ሲያነሳቸው የነበሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ያስቻሉ መሆናቸውን ገልጸዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!