በደቡብ ምዕራብ ክልል በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ የልዩ ኃይል አባላት ዕውቅና እና ሽልማት ተበረከተ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በህልውና ዘመቻው ለተሳተፉ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትና አመራሮች የዕውቅና እና የሽልማት መርሐ ግብር በቦንጋ ከተማ አካሂዷል፡፡
በመረሐ ግብሩ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አቶ ወንድሙ ኩርታና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ የህወሓት አሸባሪ ቡድን የከፈተውን ወረራ ተከትሎ መንግስትን ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ወደ ግዳጅ ቀጠና ተሰምርተው የነበሩ የክልሉ ልዩ ኃይል አባላትና አመራሮች የተሰጣቸውን ግዳጅ በቁርጠኝነት ፈፅመው ሀገርን ከማፍረስ መታደግ መቻላቸው ተነስቷል፡፡
የዕውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብሩም በግዳጅ ቀጠና ተሰማርተው ተልዕኳቸውን አጠናቀው ለተመለሱ የልዩ ኃይል አባላትና አመራሮች የተዘጋጀ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!