Fana: At a Speed of Life!

የፓኪስታን የብሔራዊ መረጃና ምዝገባ ባለሥልጣን ለኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ መዘጋጀቱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አምባሳደር ጀማል በከር ከፓኪስታን የብሔራዊ መረጃና ምዝገባ ባለሥልጣን ዳይሬክተር ሙሐመድ ታሪቅ ማሊክ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ፥ የፓኪስታን የብሔራዊ መረጃና ምዝገባ ባለሥልጣን ለኢትዮጵያ በሰነድ አያያዝ ፣ የመረጃ ደህንነት እና መረጃ አስተዳደር ዙሪያ የቴክኖለሎጂ ሽግግግር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ለአምባሳደር ጀማል ገልጸዋል።

በዘርፉ ቀልጣፋና አስተማማኝ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና አስተዳደር፣ የዜጎች ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባና አደረጃጀትና ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት ተሞክሮና ቴክኖሎጂ ማሸጋጋር በሚቻልበት ሁኔታ ሰፊ ውይይት አካሄደዋል።

አምባሳደር ጀማል በከር ፥ በፓኪስታን የተከፈተው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከለያቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህ ረገድ የፓኪስታን የዳበረ ልምድና ተሞክሮ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊና ድጋፍ ማድረግ ዙሪያም መምከራቸው ተገልጿል፡፡

የቴክኖሎጂ ሽግግሩ ትብብር ኢትዮጵያ የተያያዘችውን ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር የሚያግዝ መሆኑን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የፓኪስታን የብሔራዊ መረጃና ምዝገባ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሙሐመድ ታሪቅ ማሊክ በበኩላቸው ፥ ኢትዮጵያን በቅርበት የሚያውቁና ባለሥልጣኑ ያለውን እውቀት፣ ቴክኖሎጂና ክህሎት ለሽግግርና ድጋፍ ለማድረግ መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑን ለአምባሳደሩ አረጋግጠዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.