ኢትዮጵያ 90 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይሏን የምታመነጨው ከንፁህ እና አረንጓዴ የኃይል ምንጮች ነው – አቶ አሕመድ ሺዴ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 90 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይሏን የምታመነጨው ከንፁህ እና አረንጓዴ የኃይል ምንጮች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕምድ ሺዴ ተናገሩ፡፡
የአፍሪካ የአየር ንብረት ተነሳሽነት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
አቶ አሕመድ ሺዴ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሚያመነጨውን ኃይል ጨምሮ 90 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይሏን የምታመነጨው ከንፁህ እና አረንጓዴ የኃይል ምንጮች መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል የማምረት አቅም ቢኖራትም÷ አሁን ላይ ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት ዝቅተኛ የኃይል አቅርቦት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
የበለፀጉ ሀገራት የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን ለመቀነስ የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!