Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለጤና ተቋማት መልሶ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ለጤና ተቋማት መልሶ ግንባታ የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉትና በእንግሊዝ እና አየርላንድ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በእንግሊዝ እና ሰሜን አየርላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በአማራና አፋር ክልል በጦርነት ለወደሙ የጤና ተቋማት መልሶ ግንባታ ያሰባሰቡትን ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ለጤና ሚኒስቴር አስረክበዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ በአማራና አፋር ክልል የጤና ጣቢያዎችን ከነበሩበት በተሻለ ሁኔታ መልሶ ለመገንባት የሚውለው የትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የገንዘብ ድጋፍ የጤና ሚኒስቴር እንደደረሰው ገልጸው፥ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ገንዘቡን ለታለመለት ዓላማ በማዋል የሥራው ሂደት እስከሚጠናቀቅ ድረስ የደረሰበትን ደረጃ በየጊዜው ተከታትለው እንደሚያሳውቁም ገልጸዋል፡፡

በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መጪውን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በማስመልከት በዋዜማው “የኢትዮጵያ ቀን” በሚል በአፋርና በአማራ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ድጋፍ ለማሰባሰብ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.