Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ በቤት ልማት መርሐ ግብር በስፋት ለመግባት ተዘጋጅቻለሁ አለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገሪቱ የቤት ልማት መርሐ ግብር ላይ በስፋት ለመግባት ራሱን እያዘጋጀ መሆኑን የኢትዮዽያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፥ ኮርፖሬሽኑ የተገጣጣሚ የግንባታ ግብዓት ማምረቻ ኢንዱስትሪውን እአያስፋፋ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ፈጣን የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን ከሚጠቀሙና ከሚያመርቱ የውጭ ኩባንያዎች ጋር በሽርክና ለመስራትም ስምምነት እየፈጸመ መሆኑን ነው የገለጹት።
ኮረፖሬሽኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እያከናወነ ያለውን የመኖሪያ ቤት እድሳት መርሐ ግብር በጥራትና በፍጥነት እየገነባ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
በዚሀ ዓመትም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር 10 ሺ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችለውን የስምምንት ውል ፈጽሞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን፥ በሁለት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚያስችል አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።
የተገጣጣሚ የግንባታ ግብዓቶችን ለማምረት የሚያስችለውን ፋብሪካም በኢንዱስትሪ መንደር ገንብቶ የማስፋፊያ ስራ እያከናወነ ነው ብለዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደሚሉት፥ ኮርፖሬሽኑ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ላይ ሚናውን ለመወጣት ከቤቶች ልማት መርሐ ግብሩ በተጨማሪ፥ በሬል ስቴት ዘርፍ ለመሰማራትም ዝግጅት አጠናቋል።
አዳዲስ የግምባታ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀምና በሀገር ውስጥ ለማምረትም ከውጭ ኩባንያዎች ጋር በሽርክና ለመስራት የሚያስችለውን ስምምንት በመፈጸሙ በቅርቡ ወደ ስራ ይገባል ነው ያሉት።
አሁን ያለው የቤት ፍላጎት ከአቅርቦቱ ጋር ሲነጻጸር እጅግ ከፍትኛ ልዩነት ያለው በመሆኑ፥ የግሉን ዘርፍ አጋርነት የሚያሳድጉ ፈጣን እና ወጪ- ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን የሚጋብዙ አሰራሮችን መተግበር ይገባልም ይላሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው።
አሁን ላይ መንግሥት ለፕሮጀክቶች አፈጻጸም ከሰጠው ከፍትኛ ትኩረት አንፃር ፈጣን እና ወጪ- ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የቤት አቅርቦት ችግር በእጅጉ የሚሻሻልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም ባይ ናቸው ኢንጂነር ዮናስ።
በትእግስት ስለሺ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.