የፕላስቲክ ማሸጊያዎችን ለማምረት የሚያገለግሉ ምርቶችን ለማምረት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀመጫውን በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ያደረገው Gulf Ingot FZC የተሰኘ ድርጅት ለተለያዩ የመጠጥ እና የውሃ ማሸጊያነት የሚያገለግሉ የፕላስቲክ ማሸጊያዎችን ለማምረት የሚያገለግሉ ምርቶችን ለማምረት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ተፈራረመ።
ድርጅቱ በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ 11 ሺህ 000 ሜትር ካሬ ሼድ በመከራየት ነው ስራውን የሚሰራው።
ለዚህም 5 ነጥብ 26 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መዋዕለ ንዋይ ፈሰስ የሚያደርግ ሲሆን ከ139 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሆነ የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።
ኩባንያው አሁን ላይ በኬንያ እና ሩዋንዳ ፕሮጀክቶችን በማስተዳደር ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ በምግብና በለስላሳ መጠጥ፣ በግንባታና በሪልስቴት ዘርፎች ላይ ሲሰራ የቆየ ድርጅት ነው።
በለይኩን ዓለም
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!