Fana: At a Speed of Life!

የፌዴራል፣ የክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል፣ የክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
 
የጋራ መድረኩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት ነው በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
 
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ምሥራቅ መኮንን መድረኩን በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት÷መድረኩ ለምክር ቤት አባላት እና አካላት የተደራጀ መረጃ በማቅረብ ቀልጣፋ፣ ውጤታማ እና አስተዳደራዊ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል የጋራ የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት ነው፡፡
 
በተጨማሪም መድረኩ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ጠንካራ ምክር ቤት እንዲኖራቸው ለማስቻል ያለመ መሆኑን የገለጹት የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የአስተዳደራዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ጸሐፊ አቶ ታምር ከበደ÷ ቋሚ የግንኙነት ጊዜ በመፍጠር በተለያዩ ጉዳዮች ልምድ፣ ተሞክሮ፣ እና የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ሚናው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
 
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ፣ የክልሎች እና ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች እና ተወካዮች የየምክር ቤቶቻቸውን ሥራዎች ወደ ሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ያከናወኗቸውን የለውጥ ሥራዎች እያቀረቡ መሆኑን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
 
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.