የስንዴ ምርታማነት
ኢትዮጵያ የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች ሲሆን÷ በዘንድሮው የምርት ዘመንም ከፍተኛ ውጤት ይጠበቃል።
በዚህም መሠረት፡-
በ2015 ዓ.ም ከመኸር እርሻ ምርት ስንዴን ጨምሮ ከሁሉም የሰብል ምርቶች፡- በአነስተኛ ይዞታ አርሶ አደርና አርብቶ አደር 400 ሚሊየን ኩንታል ለማምረት ታቅዷል፡፡
በበልግ ወቅት እርሻ ምርት ደግሞ 2 ሚሊየን ሔክታር በማልማት 63 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም በበጋ መስኖ ምርት ከውጭ የሚገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በተያዘው ሀገራዊ ዕቅድ ለመተግበር በበጋ መስኖ 36 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማምረት ዕቅድ ተይዟል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕመድ ከዚህ በፊት እንደገለጹት÷ የማይታረሱ መሬቶችን በማረስ በኩታ ገጠም እርሻ በስንዴ ምርት እራሳችንን ለመቻል ሰፊ ሥራዎችን እየሠራን ነው፡፡
የግብርና ልማት የዕድገት መሠረት በመሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሠራ መሆኑን እና በግብዓትና በገበያ ትስስር ውጤታማ እንዲሆን ይደረጋል ማለታቸው ይታወሳል፡፡