Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት የ4ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ አካል የሆነ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላ ዲስትሪክት በተለያዩ አካባቢዎች የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች እና ሠራተኞች በወላይታ ሶዶ÷ ዲፖ እና ግብርና ኮሌጅ መካከል በሚገኝ ለጎርፍ ተጋላጭ በሆነ ቦታ ላይ ችግኝ ተክለዋል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ በመርሐ ግብሩ እንደገለጹት÷ ምርታማነትን በመጨመር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተለይ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች መትከል ጉልህ ሚና አለው።
ከውጪ የሚገቡ የተለያዩ ምርቶችን እዚሁ በሀገር ውስጥ በማምረት መተካት የሚያስችል በመሆኑም ሁሉም ዜጎች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላ ዲስትሪክት አመራሮች እና ሠራተኞች÷ በአሰላ ቀሉምሳ እርሻ ምርምር ተቋም ቅጥር ጊቢ ከ7ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለዋል፡፡
እንዲሁም የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመከራሮችና ሠራተኞች በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተገኝተው አራተኛውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከልና የአረጋውያንን ቤት በማደስ አከናውነዋል።
የቱሪዝም ኢንስቲትዩት አመራርና ሠራተኞች በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በጥንታዊ እና ታሪካዊ በሆኑት የፖርቹጋል ድልድይ እና በደብረ ሊባኖስ ገዳም ችግኝ ተክለዋል፡፡
ላለፉት ሦስት ዓመታት በተለያዩ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ከተተከሉ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞች 80 በመቶ የሚሆኑት መጽደቃቸው እና በቀጣይም በሀገሪቱ በተለያዩ የቱሪስት መዳረሻና ቅርስ መገኛ ቦታዎችን በአረጓዴ የማልበስ ሥራውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.