Fana: At a Speed of Life!

የጋራ ምክክር ፎረም የአሠራር መምሪያ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል፣ የክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች የሥራ ኃላፊዎች እና ተወካዮች የጋራ ምክክር ፎረም የአሠራር መምሪያውን አጽድቀዋል፡፡
የአሠራር መምሪያው፣ በሕግ አወጣጥ፣ በክትትል እና ቁጥጥር፣ በሕዝብ ውክልና እና በሙያዊ እና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች የተሻሉ ምክክሮችን፣ በለውጥ ሥራዎች አተገባበር፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና በሕዝብ ተሳትፎ የልምድ ልውውጦችን እና ተሞክሮዎችን በማስፋት ጠንካራ የምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶችን ለመፍጠር ያለመ የአሠራር መምሪያ መሆኑን ተገልጿል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት፣ የክልሎች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች የፎረሙ አባላት መሆናቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ፣ የክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጽሕፈት ቤቶች የስራ ኃላፊዎች እና ተወካዮች በመምሪያው ላይ ከተወያዩ በኋላ በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.