የናይጄሪያ ህግ አውጪ እና አማካሪዎች ልዑካን ቡድን በምስራቅ ሸዋ ዞን የሚገኙ የግብርና ስራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይጄሪያ ህግ አውጪ እና አማካሪዎች ልዑካን ቡድን በምስራቅ ሸዋ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ መንግስት ንብረት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ መንግስት የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን የህብረተሰቡን እና የአርሶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ልዑክ ቡድኑ በምሰራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ በሸራ ዲባንዲባ ቀበሌ በክላስተር እየለማ የሚገኘውን የአቮካዶ ማሳ መጎብኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡