Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመስተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ምክር ቤቱ የአደጋ ስጋት መልሶ ማቋቋም ጥበቃ ፈንድ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ተገቢው ማስተካከያ ተደርጎ እንዲጸድቅ ወደ ክልሉ ምክር ቤት መርቷል፡፡
በተጨማሪም የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ሃላፊነትና ተግባር ለመወሰን የተዘጋጀ ደንብ እና የምርጥ ዘር ድርጅት ተቋም ለማቋቋም የተዘጋጃ ደንብ ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ደንቦቹ ጸድቀው ስራ ላይ እንዲውሉ መወሰኑን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.