Fana: At a Speed of Life!

በፋይናንስ ዘርፍ ላይ በተሠራው ሥራ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዓለምአቀፋዊ ጫናዎችን ተሻግሮ ዕድገት ማስመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት የፋይንስ ዘርፉ ላይ በተሰራው ስራ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የወቅቱን ዓለምአቀፋዊ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ተሻግሮ ዕድገት ማስመዝገብ መቀጠሉን የብሔራ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ገለጹ፡፡

በፋይናንስ ዘርፍ ላይ የተመዘገቡትን ዕድገቶች እና ቀጣይ አቅጣዎች የሚገመግም መድረክ ተካሂዷል፡፡

ግብርና፣ ኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት ዘርፎች ለውጥ ማሳየት የቻሉ ዘርፎች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ የባንኩ ዘርፍ ፈጣን ዕድገት ማስመዝገቡ ነው የተጠቆመው፡

በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት 43 ሚሊየን ብር መሰብሰቡ የተገለጸ ሲሆን፥ ዕድገቱም ከታቀደው በላይ እንደሆነና በመቶኛ ሲሰላም 150 በመቶ መድረሱ ተጠቁሟል፡፡

የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥርም 16 ሚሊየን መሻገሩ ነው የተመላከተው፡፡

የባንኮች ቁጥር ቀድሞ ከነበረው በ12 መጨመሩ እና በአጠቃላይም 30 መድረሳቸው ነው የተነገረው፡፡

በተጨማሪም የማይክሮ ፋይናንስ የተቋማት ቁጥርም 40 የደረሰ ሲሆን የኢንሹራንስ ተቋማት ቁጥር ደግሞ 18 ደርሷል፡፡

ወደ 61 በመቶ የደረሰው የባንኮች ቅርጫፎች ዕድገት በቁጥር ሲገለጽ ከ5 ሺህ 564 ወደ 8 ሺህ 944 ደርሷል ተብሏል፡፡

ጠቅላላ የባንኮች የሀብት መጠንም ከ1 ነጥብ 3 ትሪሊየን ብር ፥ ወደ 2 ነጥብ 5 ትሪሊየን ብር ደርሷል፡፡

የባንኮች የብድር መጠን ከ952 ቢሊየን ወደ 1 ነጥብ 7 ትሪሊየን ከፍ ብሏል፡፡

የባንክ ደብተር የከፈቱ ሰዎች ቁጥርም ከ40 ሚሊየን በላይ ሆኗል፡፡

የተጣራ የባንኮች ዓመታዊ ገቢ ከ22 ቢሊየን ወደ 49 ነጥብ 9 ቢሊየን ከፍ ማለቱ ነው የተገለጸው፡፡

በኃይለኢየሱስ ስዩም

 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.