Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የስራ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሁለተኛውን ሀገር አቀፍ የስራ ጉባኤ እያካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ጉባኤው “ዘላቂ ስራ ለብሩህ ነገ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል÷ ጉባኤው ተደራሽ የሆነና ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መድረኩ 1 ሺህ የሚሆኑ ከፍተኛ የስራ ቀጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎችን፣ የስራ ገበያው ተወካዮችን፣ በስራ ፈጠራ ላይ የሚሰሩ ተቋማትን እና ስራ ፈላጊዎችን እንደሚያገናኝ ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.