መንግስት 8 የስኳር ፋብሪካዎችን ለጨረታ አቀረበ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደግል ለማዛወር በወጣው ጨረታ ባለሐብቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ።
መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ የተለያዩ ማሻሻያዎችን አድርጎ ወደ ስራ ገብቷል።
ከዚህ ውስጥም የግሉ ዘርፍ በስኳር ኢንዱስትሪው የሚያደርገውን ተሳትፎ ለማሳደግ በዘርፉ ማሻያዎች ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።
ከዚህ አንጻርም የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሐብቶች የስኳር ፋብሪካዎችን ወደግሉ ዘርፍ ለማዛወር በወጣው ጨረታ እንዲሳተፉ ጥሪውን አቅርቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!