በነጌሌ አርሲ ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እየተሰጠ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነጌሌ አርሲ ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን የነጌሌ አርሲ ጠቅላላ ሆስፒታል እና ሜዲካል ኮሌጅ አስታወቀ።
ሆስፒታሉ ከህንድ ባስመጣቸው የዘርፉ ሀኪሞች ነው 2 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው።
የነጌሌ አርሲ ጠቅላላ ሆስፒታል እና ሜዲካል ኮሌጅ ስራ አስኪያጅ ዶክተር በላይነህ ለታ÷ ነፃ የህክምና አገልግሎቱ በቀን ከ250 እስከ 300 የሚሆኑ የአይን ታማሚዎችን በማከም ለአንድ ሳምንት እንደሚቆይ ተናግረዋል፡፡
ስራ አስኪያጁ የአይን ሞራ ግርዶሽ በተለያዩ አካባቢዎች አይነ ስውርነትን በማስከተል ለበርካታ ሰዎች ፈተና ሆኖ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
አሁን ላይ የተጀመረው ነጻ የህክምና አገልግሎትም መሰል ችግር ላለባቸው ዜጎች እፎይታ የሚሰጥ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
የነጌሌ አርሲ ጠቅላላ ሆስፒታል እና ሜዲካል ኮሌጅ ባለቤት ዶክተር ጉደታ ሂኒካ በበኩላቸው÷ለአይን ሞራ ግርዶሽ የተጋለጡ ዜጎች ህይወታቸው ከመመሰቃቀሉ ባለፈ በቤተሰቦቻቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ጠቁመዋል፡፡
ሆስፒታሉ የአይን ሞራ ግርዶሽ የሚያስከትለውን ማህበራዊ ቀውስ በመገንዘብም ታማሚዎች ነጻ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረጉን አንስተዋል፡፡
በጀማል ከዲሮ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!