Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ የወደብ ባለስልጣን ልዑካን የሞጆ ወደብና ተርሚናልን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬያ የወደብ ባለስልጣን ልዑካን ቡድን የሞጆ ወደብና ተርሚናልን በዛሬ ዕለት ጎብኝተዋል።
 
የልዑካን ቡድኑ የጉብኝት ዓላማ ባለስልጣኑ አዲስ ለሚያለማው የላሙ ወደብ ከኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት(ኢባትሎአድ) የልምድ ተሞክሮ ለመውሰድ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
ቡድኑ የወደብና ተርሚናሉን የተለያዩ የስራ ክፍሎች የጎበኙ ሲሆን÷ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይም ከድርጅቱ አመራሮች ማብሪያ ተሰጥቷቸዋል።
 
የኢባትሎአድ የወደብና ተርሚናል ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ምህረተአብ ተክሉ÷ የኬያ የወደብ ባለስልጣን የላሙ ወደብን ለኢትዮጵያ እና ለአፍሪካዊያን ክፍት ለማድረግ ዕቅድ እንዳላው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
ይህም ወደፊት በኢትዮጵያና ኬንያ መካከል የሚደረጉ የጋራ ስምምነቶች ወደቡን ለመጠቀምና በተለይም ቡናን ኤክስፖርት ለማድረግ ከጂቡቲ ወደብ በተጨማሪ በአማራጭ ለመጠቀም ጥሩ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል።
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.