በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከ349 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 158 ፕሮጀክቶች ተመረቁ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከ349 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 158 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የወጣቶች ስብዕና መገንብያ ማእከላት፣ የደረቅ ቆሻሻ ጊዜያዊ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች፣ የፖሊስ አባላት መኖሪያ፣ የጤና እና የትምህርት ተቋማት ይገኙበታል፡፡
እንደዚሁም የጌጠኛ ድንጋይ መንገድ፣ ድልድዮች፣ የማህብረሰብ ፖሊስ ማዕከላት እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማውና የክፍለ ከተማው አመራሮች መገኘታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል ከንቲባ አዳነች የአቃቂ ዞናል ስታዲየም ግንባታን ጎብኝተዋል፡፡