በመዲናዋ ነገ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በነገው ዕለት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡
ነገ ነሃሴ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት እና አምባሳደር አካባቢ የሚወስዱ መንገዶች በሥራ ምክንያት ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
• ከሴንጆሴፍ መብራት ወደ ሃራምቤ ሆቴል
• ከኢሚግሬሽን ወደ ፍልውሃ
• ከፍል ውሃ ወደ ኢትዮጵያ ሆቴል
• ከጤና ሚኒስቴር ወደ ፍልውሃ
• ከለገሃር ወደ ፍልውሃ የሚወስዱት መንገዶች ሥራው እስከጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ይህን በመገንዘብ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያመላክቷቸው አቅጣጫ መሰረት ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!