የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን ማጣሪያ ዛሬ ከሩዋንዳ ጋር ይጫወታል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጨዋታውን ዛሬ 10 ሰዓት ላይ ከሩዋንዳ አቻው ጋር ያደርጋል፡፡
የቻን የመጨረሻ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ በታነዛኒያ ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመሀል ክፍል ተከላካዩ ያሬድ ባየህ መጎዳቱን ተከትሎ÷ በምትኩ የፋሲል ከነማው አስቻለው ታመነ በስብስቡ ተካቷል፡፡
የመልሱ ጨዋታ ከቀናት በኋላ ሩዋንዳ ላይ ይካሄዳል፡፡