Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ ከ62 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የግብርና ግብዓቶች አቅርቧል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ62 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የግብርና ግብዓቶች እና የእርሻ መሣሪያዎች ለተጠቃሚዎች ማቅረቡን ገለጸ፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም የተቋሙን የ2014 አፈጻጸም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸው በ2014 በጀት ዓመት ከ14 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በምርጥ ዘር በመሸፈን 282 ሺህ ኩንታል የሚሆን ምርት መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በበጀት ዓመቱ 12 ሚሊየን 876 ሺህ 620 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ፣ 1 ሚሊየን 59 ሺህ 821 ሊትር ፈሳሽና 68 ሺህ 170 ኪሎ ግራም ዱቄት አግሮኬሚካል ለተጠቃሚዎች ማቅረቡን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማም 3 ሺህ 870 የኬሚካል መርጫ መሣሪያ ለአርሶ አደሩ፣ በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶችና ለሌሎች ተጠቃሚ አካላት ማቅረቡን ነው አቶ ክፍሌ ወልደማርያም የገለጹት።

ኮርፖሬሽኑ 46 ትራክተሮችን ከውጭ ሀገራት በማስመጣት ለተጠቃሚዎች ማቅረቡን ጠቅሰው÷ በ2014 ወደ ውጭ ከተላከ ምርት 1 ሚሊየን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር ገቢ መግኘቱንም ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.