አቶ አሕመድ ሺዴ ከሳዑዲ ዓረቢያ ልዑክ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ዶክተር ፈህድ አልሁመይዳኒ እና ከሳዑዲ የልማት ፈንድ ልዑካን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ የሁለቱን ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል፡፡
በዕለቱም በኢትዮጵያ መንግሥት እና በሳዑዲ የልማት ፈንድ መካከል የብድር ማራዘሚያ የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!